ከዳር ቋሚ ሆኖ

9 5 0
                                    

ከዳር ቋሚ ሆኖ አየሁ ጣት ሲቀስር
ህሊናውን ሽጦ  በንዋይ ሲከብር
ከሰው እየወረደ ክብሬ ይበልጣል ብሎ
የሞተውን ሲያድን የኖረውን ገድሎ
አየሁ....
የራሱን ገንብቶ የሰዉን ቤት ሲያፈርስ
እርሱ ንፉግ ሆኖ ከሌላው ሲቋደስ..
በአፉ ያራገባት ሀገር ስታቃጥል
በተግባሩ አንሶ በስልጣን ሲከብር
እርሱ በቀሰረው ሰው ሰላሙን ሲያጣ
የልጅ ወዙ ወዝቶ የእናት ሲገረጣ
ከላይ እያንዣበበ ዘመንን ሲያስቆጥር
በተራ አሉባልታ ሰው ከሰው ሲያናቁር
አየሁ ከዳር ቋሚን ሁሉ.....
ህግ ሳይሆን ስልጣን እንደሚዳኛቸው
ጥያቄዎች ሁሉ መልስ እንደሌላቸው
ከዳር ቋሚ ሆኖ ይስቃል ተደስቶ
ከጎደለው መአድ በግፍ ሆዱን ሞልቶ
ጣትም ተቀሳስሮ ስራው ተደበቀ
ከገሀዱ ይልቅ ህቡዕ ቃል በለጠ
ዳግም ላይነሳ ስሙም ተቀበረ
ስራዎቹ ሁሉ በሰው ተመካኘ
ንፁሁን ወንጀለኛ አድርገው ሲገፉ
እማኝን ፈልገው አንተ/ቺ ሲባባሉ
አጅሬ እንትና ከዳር ቋሚ ሆኖ
የአይን እማኝ ተባለ ተወክሎ

✍ ተፃፈ በሊያ አበበ

https://youtu.be/8oDGjkkDa8A

enuye1995

Joined HandsWhere stories live. Discover now